ግብፅ በፍልስጤም-እስራኤል ግጭት ዙሪያ አለም አቀፍ የመሪዎች ጉባኤ ጠርታለች።

ካይሮ ሁኔታዉን ለማረጋጋት ማንኛውንም ጥረት ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ተናግረዋል።

በጋዛ ሰርጥ የሚታየውን ወታደራዊ ግጭት ለመቀነስ ግብፅ በፍልስጤም ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለሚደረገው አለም አቀፍ አህጉራዊ ጉባኤ ግብዣ አቅርባለች፡፡

በፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ የተመራው የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ስብሰባን ተከትሎ ግብፅ የፍልስጤምን ጉዳይ ለመፍታት እና የወደፊት ሁኔታ ሊያስተካክል የሚችል አለም አቀፍ ጉባኤን ለማዘጋጀት ፍላጎት አሳይታለች ነዉ የተባለዉ፡፡

በስብሰባዉ ተባብሶ የቀጠለዉን ጦርነት እና በሲቪሎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማስቆም ከዓለም አቀፍ እና ክልላዊ አጋሮች ጋር የሚደረገውን ግንኙነት እና ፤እንዲሁም አስፈላጊውን እርዳታ ለማድረስ ከእነዚህ የእርዳታ ድርጅቶች ጋር የሚኖራትን ግንኙነት አጠናክሮ ለመቀጠልም ቃል ገብተዋል ነዉ የተባለዉ፡፡

አል ሲሲ “የፍልስጤም ጉዳይ በሁለቱ መንግስታት ንግግር የሚመጣ መፍትሄ ካልሆነ በስተቀር ምንም አይነት ሌላ መፍትሄ የለዉም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ግብፅ መረጋጋትን ለማምጣት እና እውነተኛ የሰላም ሂደትን ለማስጀመር ማንኛውንም ጥረት ለማድረግ ዝግጁ መሆኗንም አፅንዖት ሰጥተዋል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ጥቅምት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *