እግረኞችን ለመቅጣት የወጣው አዋጅ የወጣው በ2009 ዓ.ም ነበር፡፡
በኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋ የሚያደርሰውን ውድመት ለመከላከል እና ለመቀነስ የመንገድ ደህንነት ደንብ 359 /2009 መውጣቱ ይታወቃል።
በዚህ ደንብ እግረኞች የመንገድ ደህንነት ህግ ተላልፈው ሲገኙ ቅጣት እንደሚጣልባቸው አስቀምጦ ነበር።
ይህ እግረኞችን በተመለከተ የተደነገገው ደንብ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ተፈጻሚ ማድረግ እንዳልተቻለ ኢትዮ ኤፍ ኤም አረጋግጧል።
የኢትዮጵያ የመንገድ ደህንነት መድን ፈንድ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዮሃንስ ለማ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ ደንቡ እንዳይፈጸም ምክንያት የሆነው በሃገሪቱ በቂ መሰረተ ልማት ባለመኖሩ ነው፡፡
በሃገሪቱ የተመቻቸ የእግረኛ መንገድ ሳይኖር እግረኞች ላይ ቅጣት መጣል አግባብነት የለውም ሲሉም ተናግረዋል።
አቶ ዮሃንስ በአብዛኛው ለእግረኛ ተብሎ የተሰራው መንገድ ንግድ የሚከናወንበት፣ማስታወቂያ የተሰቀለበት ሆኖ ነው የሚገኘው፤ በዚህ የተነሳም ደንቡን መተግበር አልተቻለም ብለዋል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 09 ቀን 2016 ዓ.ም
