ዳሸን ባንክ እና ሸዋ ሱፐር ማርኬት ስጦታ መሰጠት የሚያስችል ካርድን ይዘው መተዋል።
ዳሸን ባንክ ከሸዋ ሱፐር ማርኬት ጋር በጋራ በመሆን ወደ ስራ የገባው ይህ ዘመናዊ የስጦታ ካርድ ሸማቾች በካርዱ ባላቸው የገንዘብ መጠን ከሸዋ ሱፐር ማርኬት የሚፈልጉትን ግዢ መፈፀም የሚያስችላቸውን አገልግሎትን ይሰጣል።
በዚህ የስጦታ ካርድ የሚሞላው አነስተኛው የገንዘብ መጠን አንድ ሺ ብር ሲሆን ካርዱን ከሌሎች ካርዶች ለየት የሚለው የዚህ የስጦታ ካርድ በአገልግሎት ላይ መዋል ለደንበኞች ከሚሰጠው ጠቀሜታ በተጨማሪ ለግዢ ብቻ ሻጮች ዕለታዊ ሽያጫቸውን እንዲያሳድጉ ዕድል እንደሚፈጥር ተነግሯል ፡፡
ይህን ካርድ ለመጠቀም ደንበኞት የዳሸን ባንክ የሂሳብ ቁጥር ሳይኖራቸውና ስማቸው በካርዱ ላይ ሳይጠቀስ መጠቀም ይችላሉ።
ደንበኞች ካርዱን ከመጠቀማቸው በፊት (ካርዱን ሲያወጡ) የካርድ ቁጥሩንና ስማቸውን ወደ 8833 በመላክ ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል ተብሏል ፡፡
ዳሸን ባንክ ደምበኞቹ ደህንነቱ የተጠበቀ የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዲያከናውኑ እና ያለ ጊዜ ገደብ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ሲሆን የሀገር ውስጥ የቅድመ ክፍያ ካርዶችን (ኮብራንድድ ካርዶች)፣ የሀገር ውስጥ ወጪ ማድረጊያ ካርዶችን (የኤቲኤም ካርዶች) እንዲሁም አለም አቀፍ ካርዶችን ለደምበኞቹ እያቀረበ እንደሚገኝ ባንኩ አስታውቋል።
በየውልሰው ገዝሙ
ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም
