የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን የሃሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር ስርጭት ለመከላከል ከፌስቡክና ቲክቶክ ጋር እየተነጋገርኩ ነው አለ፡፡

ባለስልጣኑ ከፌስቡክ እና ቲክቶክ በተጨማሪም ከኤክስ የቀድሞ ቲዉተር እና ዩትዩብ ጋርም በሀሰተኛ መረጃ እና ጥላቻ ንግግር ዙሪያ ስራዎች መጀመሩን አስታዉቋል።

የመገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን የህግ አገልግሎት ክፍል ባለሙያ የሆኑት ቆንጂት ታምራት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭቶችን ለመግታት በጋራ ለመስራት የመቀራረብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ድርጅቶቹ ከራሳቸዉ የኮሚኒቲ ስታዳርድ ባሻገር፣ በአዋጅ በተቀመጠዉ መሠረት በፕላትፎርሞቹ የሚደረጉ ማንኛዉም አይነት ሀሰተኛ መረጃን እና የጥላቻ ንግግርን፣ ከፕላትፎርሙ ላይ እንዲያወርዱ የሚያደርግና ተጠያቂነት የሚረጣገጥበት ስራዎችን ለመሰራት የሚያደርግ ጅምሮች መኖራቸዉን አስረድተዋል።

በአዎጅ ቁጥር 1185/2012 በመገናኛ ብዙሀን፣በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎችና መሰል ሚዲያ ፕላትፎርሞችን በመጠቀም፣ የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃዎችን የመቆጣጠር ስልጣን ከተሰጣቸዉ ተቋማት አንዱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ነዉ።

ባለስልጣኑ በቅርቡ ባቀረበዉ ሪፖርት የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃ፣ የዜጎችንና የሀገርን ሁለንተናዊ ደህንነትና ሰላም በሚያናጋ እና በሚያባብስ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስታዉቋል።

በአሁን ሰዓት በባለስልጣኑ ተመዝግበዉ ዕዉቅና ኖራቸዉ የሚሰሩ 57 የበይነመረብ መገናኛ ብዙሀን ብቻ ናቸዉ።

በአቤል ደጀኔ

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.