ያለ ነዳጅ ደግሞ በከፍተኛ የእርዳታ ፍላጎት ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ጋር መድረስ አይቻልም።ያለ ነዳጅ ምንም አይነት ሰብዓዊ ድጋፍ ልናደርስ አንችልም ሲል ገልጿል።
ድርጅቱ በፅሁፍ በሰጠው መግለጫ ያለነዳጅ ውሃ የለም ፣ ሆስፒታል ፣ ዳቦ ቤቶች አይኖሩም ። ሰብዓዊ ድጋፍም ማድረስ አንችልም ሲል አስታውቋል ።
ድርጅቱ አክሎም በሰዓታት ልዩነት እየጨመረ የመጣውን የጋዛ ነዋሪዎችን ፍላጎት ያለ ነዳጅ ማሟላት አንችልም ፤ይህ ደግሞ በፍጹም ሊሆን አይገባውም ብሏል።
ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በተለይ ደግሞ ነዳጅን የሚቆጣጠሩ አካላት ወደ ጋዛ ሰርጥ ነዳጅ እንዲገባ በመፍቀድ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ ሊያደርጉ ይገባል ሲል አሳስቧል።
በእስከዳር ግርማ
ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም
