በአዲስ አበባ እና አካባቢዉ ባለፉት ሶስት ወራት በደረሱ 133 አደጋዎች የ13 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 23 ሰዎች ከባድና ቀላል አደጋዎች እንዳጋጠማቸው
የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
ጉዳት ከደረሰባቸዉ ሰዎች መካከል ስምንቱ የእሳት አደጋ ሰራተኞች መሆናቸውንም ተጠቁምል።
ከደረሱት አደጋዎች ዉስጥ 73 የእሳት አደጋዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 60 አደጋዎች በጎርፍ እና ከግንባታ ጋር የተገናኙ አደጋዎች መሆናቸውን አቶ ንጋቱ ነግረውናል።
በደረሱት አደጋዎችም ከ377 ሚሊየን 577 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት መድሙን እና በአንጻሩ የአደጋ መቆጣጠር ሰራተኞች ባደረጉት ጥረት በአደጋ ዉስጥ የነበሩ 18 ሰዎችን እና 4.9 ቢሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉ ተነስቷል።
109 አደጋዎች የደረሱት በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆኑ ቀሪ 24 የሚሆኑ አደጋዎች በሸገር ከተማ ያጋጠሙ ናቸው።
ከደረሱት የእሳት አደጋዎች ዉስጥ 25 የንግድ ቤቶች ላይ ሲሆን 21ዱ ደግሞ የመኖሪያ ቤቶች ላይ መሆኑ ተገልጿል።
በእሌኒ ግዛቸው
ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም
