በጉራጌ ዞን ከ18ሺህ በላይ ህጻናት ለምግብ እጥረት መጋለጣቸው ተነገረ።

የምግብ እጥረት ችግር የገጠማቸው ህጻናቱ በአሁኑ ሰዓት ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች እየተጋለጡ ይገኛሉ ነው የተባለው።

የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በዞኑ ለምግብ እጥረት ችግር የተጋለጡትን ህጻናት ልየታ በማድረግ ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል።

ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘም በአሁኑ ሰዓት 36 ህጻናት ለበሽታ መጋለጣቸውን ነው ሃላፊው የተናገሩት።

በዞኑ እየተስተዋሉ ያሉ የድንገተኛ ወረርሽኝ አደጋዎች በአፋጣኝ ለመከላከል ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በምግብ እጥረት ምክንያት ትውልዱ የከፋ ችግር ላይ እንዳይወድቅ ሁሉም ድጋፍ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

በዞኑ በአሁን ሰዓት ድንገተኛ በሽታዎች፣ የኮሌራና የወባ በሽታዎች እና በስነ ምግብ እጥረት ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎች ለመከላከል ሰፊ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ሃላፊው ተናግረዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.