በጋዛ አምቡላንሶችን ተክተዉ አህዮች ተጎጂዎችን ማጓጓዝ መጀመራቸዉ ተሰማ::

እስራኤል በጋዛ እየወሰደች ባለችዉ ጥቃት መሰረታዊ አገልግሎቶች መቋረጣቸዉን ተከትሎ፤ የተጎዱትንና የሞቱ ዜጎችን በአህዮች ወደ ሆስፒታል ማጓጓዝ መጀመሩ ተነግሯል፡፡

በከተማዋ የሚገኘዉ የአል ሺፋ ሆስፒታል ዳይሬክተር እንዳስታወቁት የመገኛኛ ዘዴዎች በመቋረጣቸዉ የተጎድ ዜጎች በእህያ እየተጫኑ ወደ ሆስፒታል እየመጡ ነዉ ብለዋል፡፡

ዛሬ ጠዋት በተወሰነ ደረጃ የስልክ አገልግሎት የተጀመረ ቢሆንም አምቡላንሶችን ለማግኘት እንደተቸገሩ ዳይሬክተሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመገናኛ ዘዴዎች መቋረጣቸዉን ተከትሎ በጋዛ ሁኔታዎች እንደከፉ እየገለጸ ይገኛል፡፡

በጋዛ ሰርጥ የኢንተርኔት እንዲሁም የስልክ አገልግሎቶች መቋረጣቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አስታዉቀዋል።
ከመገናኛ ዘዴዎች መቋረጥ በተጨማሪ በጋዛ እየደረሰ ያለው የማያባራ የአየር ጥቃትም ስጋት እንዳሳሰባቸው በኤክስ ገጻቸው አስፍረዋል።

በአባቱ መረቀ

ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *