በሃገራችን 76 የሚሆኑ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪዎች የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል መባሉ ተገልጿል፡፡

በኮንትሮባንድ እና በህግ ሽፋን አማካኝነት ወደ ሃገር ውስጥ በሚገቡ የብረታ ብረት ምርቶች ምክኒያት በሃገራችን የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን የመጥፋት አደጋ እንደተጋረተባቸው የኢትዮጵያ መሠረታዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች ማህበር አስታውቋል።

ከ76 በላይ የማህበሩ አባል የሆኑ መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች በአመት ከ10 ሚሊየን ቶን በላይ የማምረት አቅም እንዳላቸው የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ሙልጌታ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እነጂ በኮንትሮባንድ እና ህግን ሽፋን ባደረገ መልኩ ከውጭ የሚገቡ ያለቀላቸው ምርቶች፤ የሃገራችን ኢንዱስትሪዎች ከማምረት አቅማቸው 20 በመቶ ብቻ እንዲያመርቱ እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡

ይህም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ላይ የመጥፋት አደጋን ጋርጧል ሲሉ አቶ ሰለሞን ገልጸዋል፡፡

ከውጭ በኮንትሮናንድ እና በህግ ሽፋን የሚገቡ የብረታ ብረት ምርቶች ደረጃቸው ዝቅ ያለ እና ከማምረቻ ዋጋ በታች የሚሸጡ በመሆናቸው የሃገር ውስጥ አምራቾችን እያዳከሙ መሆናቸውን አስተዋል፡፡

አክለውም አንዱስትሪዎቹ እየከሰሩ በመሆናቸው ከባንክ የተበደሩትን ብድር እንኳን የመመለስ አቅም እያጡ መምጣታቸውን አቶ ሰለሞን ሙልጌታ አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መሠረታዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች ማህበርም ለዚህ ችግር መፍትሄ ፍለጋ በተለያዩ መድረኮች እና እስከ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጸህፈት ቤት ድረስ በደብዳቤ መጠየቁን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በቢሊየን የሚቆጠር ገቢ መንግስት እንዲያጣ የሚያደርግ እና በሃገሪቱ ውስጥ የሚገኙ አምራች እንዱስትሪዎችን ሙሉ በሙሉ ሊያዘጋ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

ስለሆነም ህጋዊነትን ሽፋን ባደረጉ ህገወጥ ተግባራት ኢንዱስትሪዎቹ ከገበያ ውጭ እየሆኑ በመምጣታቸው መንግስት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ሲል ማህበሩ ጠይቋል፡፡

መሳይ ገ/መድህን
ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *