6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል፡፡

የምክር ቤቱ አባላትም ጥያቄዎቻቸዉን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነዉ፡፡
ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከልም፡-

• በአማራ ክልል ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ አኳያ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል?

• የፕሪቶሪያው ስምምነት አፈጻጻም በምን ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው ?

• አለመግባባቶች ወደ ግጭት ከመግባታቸው በፊት የመንግሥት ዝግጁነት እንዴት ይገለጻል?

• የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመመከት ረገድ ምን እየተሠራ ነው?

• የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅና አዳዲስ በመጀመር የሕዝብን ጥያቄ ለመመለስ በመንግሥት በኩል ምን እየተሠራ ነው?

• እንደ ሀገር ካለው የባሕር ወደብ ፍላጎት ጋር በተያያዘ አንዳንድ ብዥታዎች ስላሉ ግልጽ ለማድረግ ያህል ማብራሪያ ቢሰጥ፣

• በአጠቃላይ ፀረ-ሌብነት ትግልን ከማጠናከር በተለይም አንዳንድ ለብልሹ አሠራር የሚያጋለጡ ዘርፎችን ከሌብነት በጸዳ ሁኔታ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እንደመንግሥት ያለው ቁርጠኝነት ቢገለጽ፣

• ለሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ስኬት የመንግሥት ድጋፍ ቢጠቀስ፣ የሚሉት ይገኙበታል

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *