የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ይፋ ከሚያደርጋቸዉ ሪፖርቶቹ 83 በመቶዉ ብቻ ለእዉነት የቀረበ መሆኑ ገለጸ፡፡

የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከስራ ቅጥር ጋር ተያይዞ ከየአከባቢዉ ከሚመጡ ሪፖርቶች መካከል 83በመቶዉ ብቻ ለእዉነት የቀረበ መሆኑን አስታዉቋል፡፡

ባለፉት 2 ዓመታት ሪፖርት ከተደረገዉ የስራ ዕድል ፈጠራ 85 በመቶዉ ብቻ ለእዉነት የተጠጋ 15 በመቶዉ ደግሞ ዉድቅ የሆነ መሆኑን ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ገልጸዋል፡፡

በ2015 ዓ.ም 3.5 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥረናል ያልነዉ፣ ከየክልሉ ከመጡ ሪፖርቶች 85 በመቶዉን ብቻ ወስደን ነዉ ያሉት ሚኒስትሯ፤ ሪፖርቶቹ ላይ ተመስርቶ በተደረገ ጥናት 100 በመቶ ሪፖርት ማድረግ አልቻልንም ብለዋል፡፡

ከ2016 ጀምሮ ያለዉን ግልጽ ለማድረግ ጥናት አስደርገን የተገኘዉ መረጃ እንደሚያሳየዉ ደግሞ፣ በዚህ ዓመት 83 በመቶ ብቻ ትክክል ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል፡፡

ከየአከባቢዉ የሚመጡ ሪፖርቶች የተዓማኒነት ደረጃ ምን ያህል ነዉ በሚል መረጃ የማጥራት ስራ እየሰራን እንገኛለን ነው ያሉት፡፡

ሚኒስትሯ በተጨማሪም ከሰኔ ጀምሮ ባለዉ 5 ወር ጊዜ ዉስጥ ለ1.1 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ህዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *