የዓለም ጤና ድርጅት አል-ሺፋ ሆስፒታል የሞት ዞን ሆኗል ሲል ገለጸ፡፡

በሆስፒታሉ 25 የጤና ባለሙያዎች እና አዲስ የተወለዱ 32 ጨቅላ ህጻናትን ጨምሮ 2መቶ91 ህመምተኞች መኖራቸዉንም በጉብኝት ማረጋገጡን ገልጿል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በስፍራዉ ተገኝቶ ጉብኝት ካደረገ በኋላ ስፍራዉ ‹‹የሞት ዞን›› ሆኗል ሲልም ገልጿል፡፡

ድርጅቱ የላካዉ ቡድን በሆስፒታሉ ዉስጥ ለአንድ ሰዓት ብቻ መቆየት እንደቻለ የገለጸ ሲሆን ሁኔታዉ እጅግ ከባድ ነዉ ሲልም ገልጾታል፡፡

የእስራኤል ጦር ወደ 2ሺህ 5መቶ አከባቢ ተፈናቃይ ሰዎችን ከስፍራዉ ለቀዉ እንዲወጡ ትዕዛዝ የሰጣቸዉ ቢሆንም አሁንም ድረስ በሆስፒታሉ ዉስጥ 25 የጤና ባለሙያዎች እና 32 አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ህጻናትን ጨምሮ 2መቶ 91 ህመምተኞች ይገኛሉ ብሏል ድርጅቱ፡፡

የአንዳንድ ህመምተኞች ህይወት በዚህ 2 እና 3 ቀናት ጊዜ ዉስጥ የህክምና አገልግሎት ማግኘት ባለመቻላቸዉ ማለፉንም አስታዉቋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት እና አጋሮቹ በስፍራዉ የቀሩ ህመምተኞችን፣ ሰራተኞችን እና ቤተሰቦቻቸዉን በፍጥነት ማስወጣት የሚችልበትን ዕቅድ እያዘጋጀ መሆኑንም ነዉ የገለጸዉ፡፡

እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ ጥቅምት 7 በከፈተችዉ ጥቃት እስካሁን ድረስ በአየር እና በመሬት ድብደባ 13 ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን መገደላቸዉን የአናዶሉ ዘገባ ያሳያል፡፡

በእስከዳር ግርማ

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *