በቴሌ ብር 7.21 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለፀ

በቴሌ ብር ክፍያ 7.21 ቢሊዮን ብር  መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኤሌክትሮኒክስ የመክፈያ ዘዴ በ4 ወራቱ 91 በመቶ የሚሆኑ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በቴሌ ብር ስርኣት መክፈላቸውን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ገልጸዋል፡፡

በሩብ ዓመቱ ግብራቸውን በማሳወቅ  ከከፈሉ 22,628 ግብር ከፋዮች ውስጥ 18,652 (82%) በኢ-ፔይመንት መክፈላቸው ተመላክቷል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እስካሁን 19 ባንኮችን ወደ ስርዓቱ ማካተት መቻሉ ገልፆ ሲሆን የቴሌ ብር ስርአት ከተጀመረ ጀምሮ ከ2,143 ግብር ከፋዮች 7.21 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል ሲል አስታውቋል።

ህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.