በአዲስ አበባ ጊዜያቸው ያለፈባቸው የለስላሳ እና የጁስ ምርቶች እየተወገዱ ነው።

በተለያዩ የንግድ መደብሮች የአገልግሎት ዘመናቸው ያለፈባቸው የለስላሳ እና የጁስ ምርቶች እየተወገዱ መሆኑ ተገልጿል።

የከተማው ንግድ ቢሮ ባደረገው ክትትል እና ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት፣ በተለያዩ ሱቆች ጊዜያቸው ያለፈባቸው ምርቶች እያስወገዱ እንደሚገኙ ጣበያችን አረጋግጧል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ አቶ ሰውነት አየለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በከተማዋ ንግድ ማዕከላት በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደባቸው ይገኛል ብለዋል።

በዚህም በተያዘው 2016 ሩብ አመት ከ10ሺህ በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለዋል።

እርምጃ ከተወሰደባቸው ንግድ ተቋማት መካከል የንግድ ቤታቸው የታሸገባቸው እንዳለም ነው የተነገረው።

ህብረተሰቡ በሚገበያይበት ወቅት የአገልግሎት ዘመናቸው ያለፈባቸው ምርቶች እና ተመሳስለው የሚሸጡ ምርቶችን በሚመለከትበት ጊዜ ጥቆማ እንዲያደርግም አቶ ሰውነት ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ንግድ ቢሮው ያለ ንግድ ፈቃድ በሚነግዱ ነጋዴዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።

በሄኖክ ወ/ገብርኤል

ህዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *