አትዮጵያዊያን ተሸላሚ የሆኑበት እና በአህጉሪቱ ያለውን የምግብ ደህንነት ለማረጋገጥ በሚል ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል።

በአፍሪካ ሃገራት በምርት ስብሰባ ወቅት ያለውን ብክነት በመቀነስ ለምግብ ዋስትና መፍትሔ ማምጣት ያስችላል የተባለለት የ6 ወር ስልጠና መጠናቀቁ ተገልጿል።

በግብርና የምርት ስብስባ ወቅት በተለይ በአፍሪካ ሃገራት በብክነት የሚጠፋውን ምርት ለመቀነስ በሚል ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ለተወጣጡ ሰልጣኞች የተሰጠው ስልጠና በትናንትናው እለት ተጠናቋል

የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ህዝቦች በግብርና ላይ የተመሰረተ ሕይወት ቢኖራቸውም ፣በግብርናው ላይ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ አልቻሉም ሲሉ Center African Leadership in Agriculrture(CALA) ፕሬዚዳንት ዶክተር አግነስ ካሊባታ ተናግረዋል ።

በተለይ በምርት ስብሰባ ወቀት በሚፈጠረው የምርት ብክነት የተነሳ ሃገራቱ ከምርታቸው ውስጥ 40 በመቶውን እንደሚያጡ ገልጸዋል ።

ይህ ማለት 3 መቶ ሚሊየን ህዝቦችን መመገብ የሚችል ምግብ እንዲሁ ይባክናል ማለት ነው ብለዋል።

ይንንም ችግር ለመቅረፍ Center African Leadership in Agriculrture(CALA) ከተለያዩ የአፍረካ ሃገራት የተወጣጡ ባለሞያዎች በማሰልጠን አስመርቋል ።

የምግብ ድንህነት ለማረጋገጥ በሚል የተጀመረው ይህ ስልጠናም ከየሃገራቱ የተወጣጡ 80 ባለሞያዎችን አሰልጥኖ በብቃት ማስመረቅ መቻሉን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል ።

ስልጠናውን ከወሰዱ 80 ባለሞያዎች መካከል አስሩ እትዮጵያውያን መሆናቸውን የተገለፀ ሲሆን ኢትዮጵያውያንን ጨምር ስልጠናውን በብቃት ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በመሳይ ገ/መድህን
ህዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *