በ77,280ብር ቅድመ ክፍያ እና በ2000 ብር በሚጀምር ወርሃዊ ቁጠባ የቤት ባለቤት ሊያደርግ መሆኑን ኪ ሀውሲንግ አስታወቀ፡፡

አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ለቤት ፈላጊዎች፣ በ77,280 ብር ቅድመ ክፍያ እና በ2000 ብር በሚጀምር ወርሃዊ ቁጠባ የቤት ባለቤት ሊያደርግ መሆኑን የኪ ሀውሲንግ ፋይናንስ ሶሊውሽን ማናጀር ግሩም ይልማ ተናግረዋል።

በሀገራችን ብሎም በከተማዋ ያለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት እና የቤት ፈላጊዎች ቁጥር መበራከትን ተከትሎ፣ CHF የተሰኘ ሞዴል በመፍጠር አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች የቤት ባለቤት ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተነግሯል።

የምዝገባ ሂደቱ ህዳር 30/2016ዓ.ም የነበረ ቢሆንም በቤት ፈላጊዎች ጥያቄ መሰረት ታህሳስ 22 ቀን 2016ዓ.ም ድረስ የቤት ምዝገባው እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።

ከባለ1 እስከ ባለ 3 መኝታ ቤት ድረስ በአዲስ አበባ እሪ በከንቱ፣ በጋርመንት፣ በሀያት እና በሰሚት አከባቢዎች የሚገነቡ ሲሆን 20 ዕጣዎች ለ10 ዓመት የሚቆይ መሆኑም ተመላክቷል።

በዛሬው እለት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አማካኝነት ዕጣ በማውጣት አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ቤት ፈላጊ የማህበረሰብ ክፍሎችን የቤት ባለቤት እንደሚደረግም ተገልፆል።

ኤዜድ ሪል እስቴት ፣ላመስግን ውበቱ አፖርትመንት፣ራስ ሪል ስቴት እና ቱዋይ ኢንጅነሪንግ ጋር በጋራ በመሆን በቀጣይ አንድ አመት 100 መቶ ቤቶችን በመገንባት አነስተኛ እና ለመካከለኛ ገቢ ላላቸው የቤት ፈላጊዎች ለማስረከብ ከኪሀውሲንግ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

በዚህም መሰረት የመጀመሪያው ዕጣ ታህሳስ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ለእድለኞች የሚተላለፍ ሲሆን የሚተላለፉ ቤቶችን በከተማዋ የተለዬዩ አከባቢዎች ከአልሚዎች ላይ በመግዛት መዘጋጀቱ ተነግሯል።

በእሌኒ ግዛቸው

ታህሳስ 03 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *