በአዲስ አበባ ከተማ በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚከፈቱ የማሳጅ ቤቶች ላይ ከ15ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ጀምሮ የማሳጅ ቤቶችን እስከ ማሸግ ድረስ እርምጃ እወስዳለው ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
በመዲናዋ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በ200 ራዲየስ አቅራቢያ የሚከፈቱ የማሳጅ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ እንደሚታሸጉ እንዲሁም የ15ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልባቸው የባለስልጣኑ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
ባለስልጣኑ ከትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በትምህር ቤቶች አከባቢ የሚገኙ ማሳጅ ቤቶች ላይ ቁጥጥር እንደሚደረግ የገለጹ ሲሆን፤ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶችን ለማስከበር የህብረተሰቡም ተሳትፎ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል፡፡
እሌኒ ግዛቸው
ታህሳስ 05 ቀን 2016 ዓ.ም
