6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባው ወ/ሮ ምዕላተወርቅ ሀይሉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾሟል ።
ወ/ሮ ምዕላተወርቅ ሀይሉ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የፅ/ቤት ሀላፊ ሆነው እያገለገሉ እንደሚገኙ በምክር ቤቱ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚንስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ካቀረቡት ግለ ታሪካቸውን መረዳት ተችሏል።
ምክር ቤቱ ወ/ሮ ምዕላተ ወርቅ ሀይሉን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአበላጫ ድምፅ በውሳኔ ቁጥር 2/2016 ሆኖ አፅድቋል።
የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ምዕላተ ወርቅ ሀይሉ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በታማኝነት፣ በትጋትና በብቃት ለመወጣት በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ-ማሃላ ፈጽመዋል።
ታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም