የሕዝብ በዓላትን፣ የዕረፍት ቀናትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የቀረበው ረቂቅ አዋጅ እንዲጽደቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተላለፈ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 26ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔን አሳልፏል፡፡

ከውሳኔዎቹ መካከል የሕዝብ በዓላትን፣ የዕረፍት ቀናትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት መደረጉ ተሰምቷል፡፡

ምክር ቤቱ ተወያይቶ ውሳኔ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች የሕዝብ በዓላትን፣ የዕረፍት ቀናትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ሲሆን የሕዝብ በዓላት እና የእረፍት ቀናት ለዜጎች ሥነ-ምግባርና ስነ-ልቦና ግንባታ እንዲሁም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦዋችው ከፍተኛ በመሆኑ ሕጋዊ እውቅና መስጠት እና በብሔራዊ ደረጃ እንዲከበሩ ማድረግ የሚገባ በመሆኑ፤ ኃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ታሪካዊ ሥርዓታቸውን ጠብቀው ሊከበሩ የሚገባ በመሆኑ፤ የዜጎችን የእርስ በእርስ መልካም ግንኙነትና መተሳሰብ የሚያጎለብቱ እንዲሆኑ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል እንዲጽደቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪ የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሣ የሚከፈልበትን እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰንም በቀረበው ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቷል፡፡

በተጨማሪም በሜዳይ፣ ኒሻን እና ሽልማት ረቂቅ አዋጅ ላይ የተወያየ ሲሆን በመጨረሻ ምክር ቤቱ በአምራች ኢንዱስትሪ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ተወያይቷል፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮያዊያን
ታህሳስ 10 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *