ዶናልድ ትራምፕ እኔ እንደ ሂተለር ጨካኝ አደለሁም አሉ።

የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳት ዶናልድ ትራምፕ ይህንን ያሉት ከስደተኞች ጋር በተያያዘ ሰሞኑ ካደረጉት ንግግር ጋር በተገናኘ ትችት ማስተናገዳቸውን ተከትሎ ነው።

ትራምፕ ስደተኞች የሀገራችንን ደም እየበከሉ ናቸው እናም ለሀገራችን አያስፈልጉም ሲሉ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡

ከዚህ ንግግራቸው በኋላ በርካቶች የዶናልድ ትራምፕ ንግግር ከዘረኝነት እና ከጨካኝነት ጋር አመሳስለውት ሲተቿቸው ከርመዋል።

በርካቶች ከሂትለር ጋር ያመሳስሉኛል ያ ደግሞ ፈጽሞ ትክክል አይደለም ያሉት ትራምፕ የሂትለር ግለ ታሪክ የያዘው ዘ መኒ ካምፍ የተሰኝውን መጽሀፍም እንደማያውቁት ተናግረዋል።

የቀድሞ ፕሬዝዳንቱ ስለ ሂትለር የማውቀው አንድም ነገር የለም እኔ የሂትለር ተማሪ አይደለሁም ሲሉ ሁዝ ሄዊቲ ለተሰኘው ራዲዮ ተናግረዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ታህሳስ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.