ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ ወርቁ ህንፃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተከራይቶ በሚኖርበት ቤት ውስጥ ነው፡፡
አደንዛዥ ዕፅ በችርቻሮ እያሸገ ቤቱ ውስጥ እንደሚሸጥ እና በርካታ ወጣቶች እየመጡ እንደሚገዙ ለፖሊስ በደረሰው ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በሚኖርበት ቤት ውስጥ በተደረገ ፍተሻ በአምስት ትልልቅ ፌስታሎች ለሽያጭ የተቀመጠ አደንዛዥ ዕፅ ተይዟል፡፡
ዕፁን ከሻሸመኔ አካባቢ ከሰል በሚጭን መኪና ውስጥ ደብቆ ወደ አዲስ አበባ እንደሚያስገባም ተጠርጣሪው በሰጠው ቃል እና ፖሊስ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ፖሊስ ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ለወንጀል መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ አዋኪ ድርጊቶችን ከባለ ድርሻ እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲወገዱ ማድረግ ሲሆን በተለይም የምሽት ጭፈራ ቤቶችን ጨምሮ ሺሻ በሚጨስባቸው እና በጫት መቃሚያ ቤቶች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁሟል፡፡
የቤት አከራዮች የተከራዮቻቸውን ማንነት በሚገባ ከማረጋገጥ በተጨማሪ ባከራዩት ቤት ውስጥ ህገ ወጥ ድርጊት ተፈፅሞ ሲገኝ ለሚመለከተው አካል የማሳወቅ ግዴታ ያለባቸው ቢሆንም እንዲህ አይነት ችግሮች እንዳይከሰቱ በየጊዜው መከታተል እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲመለከቱ በቸልታ ማለፍ እንደሌለባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 15 ቀን 2016 ዓ.ም
