አመታዊዉ የቁሉቢ ቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላም እንዲከበር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ

በመጪዉ አርብ ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም የሚከበረዉ ዓመታዊ የቁሉቢ ገብርኤል የንግስ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር በቂ ዝግጅት ማድረጉን ፖሊስ መምሪያዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቋል፡፡

የድሬዳዋ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነትና ለዉጥ ስራዎች ዳይሬክተር ኮማንደር ገመቹ ካቻ ፤ በዓሉ ያለምንም የፀጥታ የትራፊክና የወንጀል ችግር እንዲከበር ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ረጅም ጊዜ የፈጀ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡

እንግዶችን ከመቀበል ጀምሮ የንግስ በዓሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ የፀጥታ ኃይሉ በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

ከድሬ ዳዋና ከሌሎችም አካባቢዎች በእግራቸዉ መጓዝ ለሚፈልጉ ተጓዦች የጸጥታ ሃይሉ ጥበቃ እንደሚያደርግላቸዉ ኮማንደር ገመቹ ገልጸዋል፡፡

በዓሉ በሚከበርበት ቁሉቢ አካባቢ የስርቆትና ሌሎች ወንጀሎች እንዳይፈጸሙ በቂ ዝግጅት ተደርጓል ተብሏል፡፡፡

መሰል ወነጀሎችን ለመከላከልም ጊዚያዊ የፖሊስ ጣቢያና ችሎት ማዕከላት እንደተቋቋሙ ሰምተናል፡፡

አሽከርካሪዎች ወደ በዓሉ ቦታ ሲጓዙ የአካባቢዉን መልዕካ ምድር ከግንዛቤ አስገብተዉ የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት በጥንቃቄ እንዲያሽከረክሩም ኮማንደር ገመቹ አሳስበዋል፡፡

በየዓመቱ በድምቀት የሚከበረዉን የቁሉቢ ቅዱስ ገብርኤል ንግስ ለማንገስ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በርካታ እንግዶች ወደ ስፍራዉ ጉዞ መጀመራቸዉንም ሰምተናል፡፡

አባቱ መረቀ
ታህሳስ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *