በእሳት አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ቀጠፈ፡፡

ሌሊት 8:03 ሰዓት ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ገርጂ ሰላም ሰፈር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በተነሳ የእሳት አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት አልፏል።

ሟቹ ብቻዉን ተከራይቶ የሚኖር ሲሆን ለጊዜዉ ምክንያቱ ባልታወቀ የእሳት አደጋ ዕድሜዉ 35 ዓመት የተገመተ ሰዉ ህይወቱ አልፏአል።

የእሳት አደጋዉ ጥሪ ዘግይቶ በመድረሱና የግለሰቡ ህይወቱ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከመድረሳቸዉ በፊት ያለፈ መሆኑ ተነግሯል።

በእሳት አደጋዉ በንብረት ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል ተብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *