የነዋሪነት መታወቂያን በህገወጥ መንገድ ሲሰሩ የነበሩ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መዉሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር አቶ መላክ መኮንን የከተማዋን የነዋሪነት መታቀዊያን በማስመሰል ሲሰሩ የነበሩ በማህበረሰቡ ጥቆማና ክትትል 13 ባለሙያዎች ላይ እና 3 የስራ ሃላፊዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።

ኤጀንሲዉ በዚህ አይነት ሌብነትና ብልሹ አሰራር ላይ የሚሰማሩ አካላትን ተከታትሎ እርምጃ መዉሰዱን እንደሚቀጥል ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቋል፡፡

በሌላ በኩል በከተማ አስተዳደሩ ከሌሎች ክልል እና ከተማሞች የሚመጡ ነዋሪዎችን በተመለከተ የሚያመጡትን የድጋፍ ደብዳቤ የሚያረጋግጡበት አሰራር ባለመኖሩ አገልግሎት መስጠት አለመጀመሩን አቶ መላክ ገልፀዋል።

ኤጀንሲዉ ለ4 መቶ 80 ሺህ የመዲናዋ ነዋሪዎች የዲጅታል የነዋሪ መታወቂያ ተጠቃሚ ማድረጉንም አስታዉቋል፡፡

በመዲናዋ ውስጥ ከሚገኙት 1 መቶ 19 ወረዳዎች 1 መቶ 4 ወረዳዎችን በመለየት የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ተጠቃሚ ማደረጉን ሰምተናል፡፡

ቀሪዎቹን 15 አዳዲስ ወረዳዎች ለሚኩራ፣አቃቂ፣ንፋስ ስልክን እና ሌሎች ወረዳዎች በዲጂታል መሰረተ ልማት ችግር ወደኋላ ተጉቷል ተብሏል፡፡

በልዑል ወልዴ

ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *