በራያ ዓዘቦ ወረዳ የማቻሬ ቀበሌ ነዋሪዎች በአካባቢው ንፁህ የመጠጥ ውሃ ባለ መኖሩ ከእንስሳት ጋር ከኩሬ እንዲጠጡ መገደዳቸውን ተናገሩ፡፡

በትግራይ በአብዛኛው አካባቢ በንፁህ የመጠጥ ውሃ ችግር ህዝቡ እየተሰቃየ እንደሚገኝም መረጃዎች እያመላከቱ ነው፡፡
በራያ ዓዘቦ ወረዳ መቻሬ አካባቢ ለዓመታት ሳይፈታ የቆየው ንፁህ የመጠጥ ውሃ ችግር ህልውናቸው ላይ አደጋ እንደሆነባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡

የመቻሬ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ሻይነ አርአያ በቀበሌው ከ13 ሺ በላይ ነዋሪዎች እንዳሉ እና እንደ መፍትሄ የተቀመጠው አንድ የውሃ ቧንቧ እየተጠቀሙ ቢሆንም ከህዝቡ ቁጥር አንፃር ሊመጣጠን እንዳልቻለ እንዲሁም ነዋሪዎቹ ለንፁህ የመጠጥ ውሃ ችግር ተጋልጠዋል ብለዋል፡፡

የራያ ዓዘቦ ወረዳ የውሃና ፍሳሽ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሲራጅ መሓመድ በበኩላቸው ከመቻሬ እና ሌሎች 10 ቀበሌዎች ጨምሮ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ችግር እንዳላቸው በመግለፅ ከጦርነቱ በፊት ችግሩን ለመፍታት የተጀመሩ ስራዎች ቢኖሩም አሁን ላይ ወደ ተግባር ባለ መግባታቸው የህዝቡ ስቃይ እንዲባባስ አድርጎታል፤ ችግሩ ከፍተኛ በመሆኑም በወረዳው አቅም እንደማይፈታ ገልፀዋል፡፡

የትግራይ የውሃና ፍሳሽ ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ታጠረ ሃዱሽ በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጠው የነበሩ የውሃ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ በቅርብ ጊዜ ይህንን ችግር ለመፍታት እንደሚሰራም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በልዑል ወልዴ

ታህሳስ 22 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *