ኢትዮ ቴሌኮም የጥር ወርን “የልብ ህሙሟን ሕጻናት ወር” በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰቢያ ሊያከናውን መሆኑን አስታወቀ::

ለአንድ ወር በሚቆየው የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የኢትዮ ቴሌኮምን እና የቴሌብርን የማህበራዊ ሚዲያዎችን በመከተልና በየቀኑ የሚለቀቁ ይዘቶችን ለሌሎች በማጋራት ለማዕከሉ ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻል ዛሬ በማዕከሉ በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል፡፡

አንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ በገቢ ማሰባሰቢያ በመርሃ ግብር ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ እስከ 1500 ብር በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ያለምንን ወጪ ማዕከሉን መርዳት ይቻላል ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በየወሩ የቴሌብር መተግበርያንና የ6710 አጭር የጽሁፍ መልዕከት የገቢ ማሰባሰቢያን በመጠቀም ድጋፎች ሲደረጉ ኢትዮ ቴሌኮም ተጨማሪ አስር በመቶ ለማዕከሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ከህዳር 2016 ዓ.ም ጀምሮ ያሉትን ተከታታይ ስምንት ወራት ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ እና የጥር ወርን “የልብ ህሙሟን ሕጻናት ወር” በሚል ማዕከሉን የሚያግዙ የድጋፍ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

በመሆኑም በየወሩ ኢትዮቴ ሌኮም እና በቴሌብር የማህበራዊ ሚዲያዎች ለሚያፈራቸው አዳዲስ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ብዛት ልክ 30 ብር እና በየቀኑ የሚለቀቁ ይዘቶች በተጋሩበት ብዛት ልክ 10 ብር ኢትዮ ቴሌኮም ለማዕከሉ ድጋፍ እንደሚያደርግም በመግለጫው ላይ ተነስቷል፡፡

ማዕከሉ ላለፉት 35 ዓመታት የነጻ የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎቶችን እየሰጠ የሚገኘው ሲሆን ለሚሰጣቸው የነጻ የልብ ሕክምና አገልግሎቶች የሚያስፈልገውን ወጪዎችን በልዩ ልዩ መንገዶች ከደጋፊ ግለሰቦች፣ ማህበራት እንዲሁም ተቋማት በድጋፍ እንደሚያገኝም ተመላክቷል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው
ታህሳስ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *