ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ደብዳቤ ጽፋል፡፡

ቦርዱ በክልሉ ለሚገኙ ሶስት መስራቤቶች ማብራርያ እንዲሰጠው ደብዳቤ መጻፉ ታውቋል፡፡

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የጎጎት የፓርቲው አመራሮች እና አባላቶች እየታሰሩ እና እየተሳደዱ መሆኑን ጠቅሶ የታሰሩበት ምክንያት እስከ ጥር 04 ቀን 2016 ዓ.ም አጣርተው እንዲያሳውቁት አሳስቧል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ፣ ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ እና ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ነው ደብዳቤው የጻፈው፡፡

ለጉራጌ ፍትህ እና ነጻነት እታገላለሁ የሚለው ጎጎት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮቹና አባላቶቹ ያለምንም በቂ ምክንያት እየታሰሩበት እንደሆነ የሚያመላክት ግልጽ ደብዳቤ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በላከው መሰረት ነው ቦርዱ ይህንን ደብዳቤ ለክልሉ የላከው ተብሏል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም ከጎጎት ፓርቲ ባገኝው መረጃ መሰረት ለእስር የተዳረጉት የፓርቲው አመራሮች እና አባላቶች መጀመርያ ከታሰሩበት ቡታዠራ ከተማ ወደ ክልሉ መቀመጫ ወደ ሆነችው ሆሳህና ከተማ መወሰዳቸው ገልጻል፡፡

ለእስር የተዳረጉት አመራሮችም ሆኑ አባላቶቹ እስካን ድረስ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡም ነው ፓርቲው ያስታወቀው፡፡

ሔኖክ ወ/ገበርኤል

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *