ኢጋድ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ፡፡

የምስራቅ አፍሪካ የበይነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ታውቋል፡፡

የጅቡቲ ፕሬዝዳንት እና የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ኢስማኤል ኦማር ጊሌህ የኢጋድ አባል ሀገራትን በሚቀጥለው ሳምንት በኡጋንዳ ለሚያደርጉት አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ ጥሪ አቅርበዋል ማቅረባቸው ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

በቅርቡ በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው አለመግባባት በተጨማሪ በሱዳን በቀጠለው ጦርነት ምክንያት ከአባል ሃገራቱ ጋር ለመምከር ቀጠሮ መያዛቸው ተገለጿል።

የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢጋድ ሀገራት በላከው ደብዳቤ ስብሰባው በቀጣይ ሃሙስ በኡጋንዳ መዲና ካምፓላ ይደረጋ ብሏል፡፡

ተሳታፊዎቹ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ውዝግብ ላይ ተወያይተው በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት እንደሚያደርጉም ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ወደብ እንድትጠቀም የሚያስችላትን ስምምነት ከሶማሌላንድ ጋር ከተፈራረመች በኋላ ነው በሶማሊያ እና በኢትጵያ መካከል አለመግባባቶች መፈጠራቸው ለቀጠናው ፈተና ነው ሲል ኢጋድ አረጋግጣዋል፡፡

ስምምነጹ በቀጣናው እና በአለም አቀፍ ደረጃ ስጋቶች መደቀኑ ታቃዋል፡፡
በዚህ ስብሰባ የሱዳን ግጭት ላይም ውይይቶች ይደረጋሉ ተብሏል፡፡

በኡጋንዳው ውይይት ላይ የሱዳን ጦር ዋና አዛዥ አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉን የሚመሩት በቅጽል ስማቸው ሂሜቲ እየተባሉ የሚጠሩት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጦርነቱን ለማቆም በቀጥታ ተገናኝተው ለመወያየት ተስማምተዋል ሲል ሱዳን ትሪቢውን ዘግቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 03 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *