በብራና ኢቨንትና ፕሮሞሽን አማካኝነት በመዲናችን አዲስ አበባ በኢትዮ ኩባ አደባባይ ከጥር 4 ጀምሮ ለማካሄድ የታቀደው የእናትዋ ጎንደር የባህል ፌስቲቫል መሰረዙ ተገለጸ::
የእናትዋ ጎንደር የባህል ፌስቲቫል አዘጋጆች ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላኩት ደብዳቤ ከጥር 4 እስከ 6/2016 ዓ.ም ለማካሄድ ታስቦ የነበረው የእናትዋ ጎንደር ፌስቲቫል ከ ጥር 14 ወዲህ ማካሄድ እንደማይችሉ መከልከላቸውን ገልጸዋል፡:

የጎንደርን ባህል ትውፊት እና ሀይማኖታዊ ፌስቲቫሎችን ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ እና መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች ለማስተዋወቅ ፌስቲቫሉ እንደተዘጋጀ የሚናገሩት አዘጋጆቹ ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ከጥር 14 በፊት ፌስቲቫሉን ማካሄድ እንደማንችል ነግረውናል ሲሉ አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡
ፌስቲቫሉ የስዕል፣ የቅርጻ ቅርጽ አውደ ርዕይ፣ የባህል አልባሳት ንግድ ትርኢት ፋሽን ሾው እንዲሁም የጎንደርን የተለያዩ ባህላዊ ትውፊቶችን ላማሳየት ያቀድ አውደ አርይ እንደነበርም ተገልጻል፡፡
በለዓለም አሰፋ
ጥር 03 ቀን 2016 ዓ.ም
