በንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ ላይ ከባድ የእሳት አደጋ መድረሱ ተሰምቷል፡፡

እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ እርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ኢትዩ ኤፍ ኤም ከአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አረጋግጧል፡፡

በንፋስ-ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በሚገኘው ንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ ላይ ከባድ የእሳት አደጋ ተነስቶ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ መሆኑን የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል።

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ የአደጋው መንስኤ እና የደረሰው ውድመት እንደደረሰን እናሳውቃለን ብለውናል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ጥር 06 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *