በኢትዮጵያ 11 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች ተጨማሪ ሚስቶች አላቸዉ ተባለ

ባሎቻቸዉ ከአንድ በላይ ሚስቶች ያላቸዉን ሴቶች የገጠር መሬት ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑንም ሰምተናል፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ከ15 እስከ 49 ዕድሜ ክልል ያሉ ሴቶች ላይ አደረኩት ባለዉ ጥናት በኢትዮጵያ 11 በመቶ የሚሆኑት ወንዶች ተጨማሪ ሌላ ሚስት እንዳላቸዉ አመልክቷል፡፡

ጥናቱን ያካሄዱት በግብርና ሚኒስቴር የህግ ባለሙያ አቶ አበባው አበበ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ከአንድ በላይ ጋብቻ የሚፈፀምባቸው ክልሎች በቀዳሚነት የተቀመጠው ሶማሌ 29 በመቶ፣ቤንሻንጉል 21 በመቶ እና ጋምቤላ 21 ናቸዉ ተብሏል፡፡

በጥናቱ አማራ ክልል 1 በመቶ፣አዲስ አበባ 2 በመቶ እና ትግራይ 3 በመቶ በመሆን የመጨረሻውን ደረጃ የያዙ ናችው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባሎቻቸው ከአንድ በላይ ጋብቻ ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ እያዘጋጀ መሆኑን አስታወቋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ከአንድ በላይ ሚስት ያገቡ አባወራዎች ሚስቶች የገጠር መሬትን በፍትሃዊነት የይዞታ ባለቤት ለማድረግ ይረዳል ተብሏል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከግብርና ሚኒስቴርና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ ላይ ከህዝብ ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

አቤል ደጀኔ

ጥር 07 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *