የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በ2016 ግማሽ ዓመት 7 መቶ 49 ሐሰተኛ መታወቂያዎችን እንደያዘ ይፋ አድርጓል፡፡
በግማሽ አመቱ አጠቃላይ 9 መቶ 8 ሐሰተኛ ሰነዶች መያዙንም ገልጿል።
ከነዚህ ውስጥ 749 ሃሰተኛ የማንነት መታወቂያ ናቸዉ፡፡ 1 መቶ 25ቱ ደግሞ የጋብቻ ማስረጃዎች ናቸው ተብሏል።
በሃሰተኛ ሰነድ የተጠረጠሩ 7 ሰዎች ላይ ክስ ለመመስረት በሂደት ላይ መሆኑን ሰምተናል፡፡
ለአለም አሰፋ
ጥር 09 ቀን 2016 ዓ.ም
