አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ከቅርብ ወራቶች በፊት ከህመሙ ጋር በተያያዘ እግሩን ማጣቱ ቢሰማም ከህመሙ ጋር ትግል እያደረገ ባለበት ሰዓት ዛሬ ጥር 14 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት ላይ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ በበርካቶች ዘንድ”ተንቀሳቃሹ ቤተ መፅሐፍት”የሚል ቅፅል ተሰጥቷል።
ሊብሮ መጋቢት 5 1957 ዓ.ም በይርጋለም የተወለደው ገነነ ስፖርትና ታሪክ አጣምሮ የሚወድ ሲሆን ለሚናገራቸውም ወይም ለሚያቀርባቸው የጽሁፍ ስራዎች በቂ ማስረጃ እና ሰነድ ይዞ ይቀርብ ነበር።
ከጽሑፍ ስራው ባሻገር በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው 2000 ዓ.ም በዛሚ ኤፍ ኤም ስፖርትና የቀድሞ ሙዚቃዎችን ታሪክ ለአድማጮች ያቀረበ ሲሆን ከ2001 እስከ 2006 ዓ.ም በኤፍ ኤም አዲስ ከአዲስ ዜማዎች ጋር ሰርቷል።
2007 ዓ.ም ደግሞ በብስራት ኤፍ ኤም “መሴ ሪዞርት” እና ሌሎች ዝግጅቶች ላይ ታሪክና ስፖርትን አዋዶ ተገልጧል። የሀገር ውስጥ ስፖርት ላይ መበርታቱን ያየ ካፍ በ2009 ዓ.ም የ60 ዓመት ጎንደል ኦፍ ሜሪት ሸልሞታል።
ስድስት ጋዜጠኞች ብቻ ያገኙትን ሽልማት በመውሰድ ገነነ ከምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው ነው።
ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ በበርካቶች ዘንድ”ተንቀሳቃሹ ቤተ መፅሐፍት”የሚል ቅፅል ተሰጥቷል።
ጥር 14 ቀን 2016 ዓ.ም
