በጋርዱላ ዞን የጊዶሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንዲት እናት 3 ልጆችን በሠላም ተገላግላለች።
ዛሬ ጥር 21 ቀን 2016 ዓም ማለዳ 2:00 ሰዓት ላይ በሆስፒታሉ በተደረገላት የቀዶ ጥገና 3 ልጆቿን በሠላም መገላገሏን በሆስፒታሉ የማህፀንና የድንገተኛ ቀዶ ጥገና ኦፊሰር የሆኑት ደመላሽ አየለ ተናግረዋል።
የተወለዱት ህፃናት 3ቱም ሴቶች ሲሆኑ፤ በአሁኑ ሰዓትም እናትቱም ሆነ የተወለዱት ሕፃናት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ በሆስፒታሉ የማህፀንና የድንገተኛ ቀደ ጥገና ኦፍሰሩ አያይዘው ገልጸዋል።
መረጃው የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው
ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም
