ዕንባ ጠባቂ በአማራ እና ትግራይ የተከሰተው “ረሃብ ወይም ድርቅ” ስለመሆኑ መንግሥት ብያኔ እዲሰጥ ጠየቀ

በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የተከሰተው ድርቅ የጉዳት መጠን ላይ ምልከታ ያደረገው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ መንግሥት ድርቅ አሊያም ረሃብ መከሰቱን በይፋ ብያኔ እንዲሰጥ ጠየቀ።

የባለሞያዎች ቡድን ወደ ሁለቱ ክልሎች በመላክ ናሙና ወስዶ የችግሩን ስፋት እንዳጣና የገለጸው ተቋሙ፤ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የደረሰ ጉዳት እና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሁኔታን በመዳሰስ የአሰራር ክፍተቶችን ማግኘቱን አመልክቷል።

የተረጂዎችን ቁጥር መለየትን ጨምሮ በተዋረድ ያሉ የመንግሥት ተቋማት የተለያዩ አሃዞችን ማውጣታቸውን የጠቀሰው ዕንባ ጠባቂ ተቋም፤ በራሱ ያሰባሰበውን ቁጥር ይፋ አድርጓል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መስተዳደር የድርቁን ተጎጂዎች ቁጥር 4.2 ሚሊዮን ቢያደርሰውም፣ የአደጋ ስጋት እና ሥራ አመራር ኮሚሽን ግን 2.2 ሚሊዮን ናቸው ብሏል።

በአማራ ክልልም የተጎጂዎች ልየታ ላይ በክልሉ አደጋ መከላከል እና የምግብ ዋስትና እንዲሁም በዞን እና በወረዳዎች መካከል አለመናበብ ከመኖሩ ባሻገር በድርቅ ምክንያት የሞተ እና የተፈናቀለ ሰው የለም እያሉ መሆናቸውን ጠቅሷል።

ኤትዩ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *