“አሁን እንዳለው ስርዓት አልበኝነትና ጥፋት እስር ቢበዛ ኖሮ ፓርክ ሳይሆን የምንገነባው እስር ቤት ነበር” አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ

በጣም ብዙ መታሰር የሚገባቸው ሰዎች በየቀኑ ይታለፋሉ” ካሉ በኃላ “ሆኖም ግን እኛ ፓርክ እንጂ እስር ቤት አለገንባንም” ሲሉም አክለዋል።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

በስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎች ጉዳይ ላይ ከመርማሪ ቦርዱ ጋር ውይይቶች መደረጋቸውን አንስተዋል፡፡

በእስር ካሉት አብዛኞቹ ወይንም በሺህ የሚቆጠሩት ተምረው ወጥተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ አሁን ላይ በመቶ የሚቆጠሩ ብቻ በእስር ቤት እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በእስር ላይ የሚገኙትም “እየተጣሩ፣ እየተማሩ ሊፈቱ ይገባል እንጂ፤ ለደሃ መንግስት እስረኞችን መቀለብ የሚያዋጣ አይደለም” ብለዋል።

ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *