ከድርድሩ ጋር በተያያዘ ለህዝብ ምንም የተደበቀ ነገር የለም ብለዋል፡፡
ከድርድሩ በኋላ ስኬቶች ተመዝገበዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ
• በትግራይ ያሉትን አየር መንገዶች ለመጠገን ግማሽ ቢሊዮን ብር ወጪ ወጥቷ ፡፡
• በቴሌ መሰረተ ልማቶች ላይ በተሰራውስራ 20ሺህ ዜጎች የቤት ለቤት ስልክ ጥገና ተደርጎላቸዋል ብለዋል፡፡
• ከኤልክትሪክ መሰረተ ልማት ጋር በተያያዘም በሁሉም ከተሞች መብራት ጥገና እንደተደረገላቸው አብራርተዋል፡፡
• ትግራይ ውስጥ ያሉ ሁሉም ሃይስኩሎች ስራ እና ትምህርት መጀመራቸውንም አንስተዋል፡፡
• ዩኒቨርስቲዎችም ወደ መማር ማስተማር ስራቸው ተመልሰዋል ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡
• ከ200 በላይ የሚሆኑ ኢንዱስትሪዎች ስራ ጀምረው ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረጉ ናቸው ብለዋል፡፡
• ለትግራይ ክልል 500 ትራክተሮች ለአርሶአደሮች እንዲከፋፈሉ ግዢ ተፈጼሟል ያሉ ሲሆን ህዝቡን ተጠቃሚ እተደረገ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት፡፡
ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም
