በሀረሪ ክልል በኮሌራ ወረርሽኝ 133 ሰዎች ሲያዙ የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል

በሀረሪ ክልል በ8 ወረዳዎች በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ 133 ሰዎች ሲያዙ የ2 ሰዎች ይህወት ሊያልፍ ማለፉን የክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ስጋት አስታውቋል፡፡

በክልሉ ከነሃሴ 3 ቀን ጀምሮ የኮሌራ ኬዞች በ9 ወረዳዎች መመዝገባቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ስጋት ዳይሪክቴር አቶ ፎዚ ሳሊህ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

በ5 ወረዳዎች ላይ የኮሌራ ወረርሽኝ ኬዞችን በአሁኑ ወቅት እየተመዘገቡ አለመሆኑ የገለጹ ሲሆን፤ በ3ወረዳዎች ላይ ግን የሚመዘገቡ ኬዞች ከቆሙ አራት ሳምንት አለመሙላቱን ተናግረው ይህም ሙሉ ለሙሉ ወረርሽኙን መቆጣጠር ተችሏል ማለት እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡

በክልሉ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽን ለመቆጣጠር በኮሌራ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የመለየት ስራ እና ምርመራዎችን የሚከናወን መሆኑን እንዲሁም 73 የውሃ ጉርጓዶችን በመለየት እንዲታከሙ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ገጠራማ ክፍል በሶፊ ወረዳ በሚገኙ ሀረዌ እና ቡርቃ ወረዳዎች ላይ በስፋት ወረርሽኙ የተከሰተባቸው አከባቢዎች ናቸው ብለዋል፡፡ አሁንም የኮሌራ ወረርሽን በስፋት በተከሰቱበት ወረዳዎች ላይ ክትትል እና ቁጥጥር እየተካሄደ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በእሊኒ ግዛቸው

የካቲት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *