በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነ የአልትራሳንውንድ የህክምና መሳሪያ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ተከፈተ፡፡

በአዲስ አበባ ጋርመንት አካባቢ በሚገኘው ሁዋጂያን ኢንዱስትሪ ፓርክ የአልትራሳውንድ የህክምና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በይፋ ተመርቋል።
ኤልስሜድ ሶሊሽንስና ሲመንስ የተሰኙ የጀርመን እና የእስራኤል ኩባንያዎች በጋራ በመተባበር ፋብሪካውን መገንባታቸው ተነግሯል።

የአልትራሳውንድ መገጣጠሚያ ፋብሪካው የተለያዩ ዓይነት ህመሞችን መመርመር የሚያስችል መሳሪያዎች የሚገጣጠሙበት ሲሆን በህክምና ዘርፍ የተሰማሩ ቴክኒሻኖች፣ መሃንዲሶችና ደጋፊ ባለሙያዎችን የሚረዳ መሆኑ ተጠቁሟል።

የኤልስሜድ የኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዳዊት ኃይሉ በፋብሪካው የሚመረቱ የአልትራ ሳውንድ የህክምና መሳሪያ መገጣጠሚያዎች በኢትዮጵያ የተሰራ (Made in Ethiopia) የሚል መለያ ብራንድ የሚጻፍባቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በእሌኒ ግዛቸው

የካቲት 04 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *