አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና የብድር ህብረት ስራ ማህበር ለሶስት የላዳ ታክሲ ማህበራት አዳዲስ መኪኖችን አስረከበ።

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር  ህብረት ስራ ማህበር ለሶስት የላዳ ታክሲ ማህበራት 69 አዳዲስ መኪኖችን አስረክቧል።

መኪኖቹን ከ15 ቀናት ባነሰ ጊዜ ማስረከቡንም የማህበሩ የኮርፖሬት ሴልስ ዲፓርትመንት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው በኃይሉ ተናግረዋል።

ማህበሩ ለ4ኛ ዙር 20 በመቶ ለቆጠቡ 69 የላዳ ታክሲ ሹፌሮች ነው መኪኖቹን ያስረከበው።

የላዳ ታክሲ ማህበራቱ ተወካዮቹም በተደጋጋሚ የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማትን የብድር አገልግሎት ለማግኘት ቢጠይቁም ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ነው ያነሱት።

ማህበሩ ከ6 ወር እስከ 10 ዓመት በሚደርስ  የክፍያ ጊዜ የብድር አገልግሎት ማመቻቸቱንም አቶ እንዳልካቸው ገልፀዋል።

በዚህ ጊዜ ውስጥም ከ9-15 በመቶ የሚታሰብ የወለድ መጠን እንደሚኖረውም ነው አቶ እንዳልካቸው የገለፁት።

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ከዛሬ 11 አመት በፊት በ20 አባላት የተመሠረተ ሲሆን አሁን ላይ የአባላቱ ቁጥር 7ሺህ ደርሷል።

የካፒታል መጠኑ ደግሞ 2 ቢሊየን ብር መሆኑም ተገልጿል።

እሰከዳር ግርማ

የካቲት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *