በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚቃጣ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቁም ኢዜማ ጠየቀ

ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ጀምሮ በአማራ ክልል በመንግሥት እና በክልሉ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖች መካከል የተከሰተው ግጭት ተከትሉ እየደረሱ ያሉ ቀውሱች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቱች መቀጠላወው ያሳስኛል ብሏል ኢዜማ፡፡

ፖርቲው ባወጣው መግለጫ ሀገራችን በተቀበለቻቸው ዓለም ዓቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጭምር ጥበቃ ሊደረግላቸው የሚገባ ሰላማዊ ዜጎችን በህይወት የመኖር መብት የሚነጥቅ ጥቃት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መፈጸሙን ከሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና ከተለያዩ አካላት ከሚወጡ መረጃዎች መረዳት እንደቻለ አሳውቋል።

በቅርብ ጊዜ በሰሜን ጎጃም ዞን በመርአዊ ፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን ሸበል በረታ እንዲሁም ምዕራብ ጎጃም ቋሪት ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ሰላማዊ ዜጎች ህይወታቸውን እንዳጡ ከተለያዩ አካላት እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ይፋ ካደረጋቸው መረጃዎች ማግኘቱን በመግለጫው አትቷል፡፡

ፓርቲው በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚደርስን ጥቃት ፍጹም እንደሚወግዘው እና በአስቸኳይ ሊቆም የሚገባ መሆኑን አንስቷል፡፡

በግጭት ውስጥ ተሳፉ ያላቸው አካላትም ለሰላማዊ ንግግር በራቸውን እንዲከፍቱ ብም ችግሮችን በውይይት በመፍታት ማኅበረሰቡ እየደረሰበት ካለው ቀውስ እንዲታደጉም ጠይቋል፡፡

በማያባራ ግጭት ማህበረሰቡን ለባሰ መከራና እንግልት ከመዳረግ ያለፈ ይህ ነው የሚባል ዘላቂ መፍትሔ ይገኛል ብለን በፍፁም እንደማያምን ኢዜማ አሳውቋል፡፡

ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመፍታት ትክክለኛውና አዋጩ መንገድ በውይይት፣ በንግግር እና በድርድር በማመን በቁርጠኝነት በመሥራት ብቻ እንደሆነ አሁንም ደግመን ለማስታወስ አንወዳለን ነው ያለው ፓርቲው በመግለጫው ፡፡

ኢዜማ በሰላማዊ ዜጎች ህልፈት የተሰማውን ሃዘን ገልጹ ለቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል። መንግሥት ይህንን ዓይነት ጸያፍ ተግባር የፈጸሙ የጸጥታ አካላትን ለይቶ አስፈላጊውን የፍትህ እርምጃ ወስዶ ውጤቱን ለሕዝብ በይፋ እንዲያሳውቅ ጠይቋል፡፡

የካቲት 06 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *