የባለ ብዙ ባለድርሻ አካላት ቡድን በአዲስ አበባ ከመከረ በኋላ ህብረቱ በአየር ንብረት አስተዳደር ላይ ያለዉን ስርዓት እንዲያጠናክር ምክረ ሀሳቦችን አቅርቧል።
ቡድኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ የአየር ንብረት ቀውስ በአፍሪካ እድገት ላይ የደቀነውን ፈተና በማንሳት የሀገራት መሪዎች በትኩረት እንዲሰሩ ጠይቋል፡፡
ህብረቱ ለአለም አቀፍ ድርድር እና ተፅእኖ አወንታዊ አበርክቶ እንዲኖረው መስራት እንዳለበትም አንስቷል፡፡
29ኛው የአየር ንበረት ለውጥ ጉባኤ ከመካሄዱ በፊት በዘርፉ ትግበራ ላይ ለውጥ እንዲመጣ በትኩረት በምክረ ሀሳቡ ላይ ቀርቧል።
የባለድርሻ አካላቱ ቡድን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የትምህርት ስርዓቱ ላይ በጥልቀት መስራት ይገባልም ብሏል፡፡
በአጠቃላይ አምስት ምክረ ሀሳቦች ለጉባኤው ተሳታፊ መሪዎች የቀረቡ ሲሆን የካርበን ንግድ ፤ የማዕድን ዘርፉ ከአፍሪካ ለአፍሪካ የሚሆንበት መንገድ ትኩረት ይሻሉ የተባሉ ጉዳዮች ናቸው።
37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ከ44ኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ በመቀጠል የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲካሄድ ይታወቃል፡፡
ሀመረ ፍሬዉ
የካቲት 07 ቀን 2016 ዓ.ም
