የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአርባምንጭ ዲሲትሪክቲ ዳይሬክተር አቶ ገረመው ወንድሙ ለኢቲዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ብልሉ የተቋረጠዉ ኤልክትሪክ ተመልሷል ፡፡
በዞኖቹ የኤሌክትሪክ ኃይል የተቋረጠው፣ ከወላይታ ዞን ወደ ጎፋ ዞን የተዘረጉ አራት የከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ ምስሶዎች በዘራፊዎች በመሠረቃቸው ነው ብለዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 26 ከተሞች ካባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት መሉ በሙሉ ተቋርጦ ነበር ።
የኤሌክትሪክ ኃይል የተቋረጠው፣ በደቡብ ኦሞ፣ በባስኬቶ፣ ጎፋ፣ አሌ እና በከፊል በጋሞ ዞኖች እንደኾነ የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአርባምንጭ ዲሲትሪክቲ ዳይሬክተር አቶ ገረመው ወንድሙ ለጣቢያችን ተናግረዋል።
በአከባቢው ከጊዜ ወደጊዜ የሌቦች መበራከት ትልቅ ተግዳሮት እንደሆነበትም ሰምተናል፡፡
ከተለያዩ የዞን ሃላፊዎች ጋር በመሆን ዝርፊያውን የመከታተልና መሰል ተግባራትን ዳግም እንዳይከሰት እየተሰራ መሆኑን ሰምተናል፡፡
በልዉል ወልዴ
የካቲት 08 ቀን 2016 ዓ.ም
