የሲውዘርላንድ ዜጎች በየወሩ የሚያገኙት የጡረታ አበል በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር በመላ አገሪቱ በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ ወስነዋል።
ሕዝበ ውሳኔው ለጡረታ ዕድሜ የደረሱ የአገሪቱ ዜጎች የጡረታ ገንዘብ ከፍ ይበል ወይስ አይበል የሚል ነበር።
የአገሪቱ መንግሥት ግን እየጫናችሁብኝ ያለው ዕዳ ከባድ ነው ሲል ምሬቱን ገልጧል።
ነገር ግን በሕዝበ ውሳኔው ድምጽ ከሰጡ ዜጎች መካከል 60 በመቶው የጡረታ አበል ከፍ እንዲል ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
በስዊዘርላንድ ከፍተኛው የጡረታ ክፍያ 2550 ዩሮ ወይም 126 ሺህ ብር አካባቢ ሲሆን ስዊዞች ግን ይህ በቂ አይደለም ይላሉ።
ስዊትዘርላንድ በዓለማችን ኑሮ ውድ ከሚባልባቸው አገራት መካከል ስትሆን፣ በተለይ ደግሞ እንደ ዙሪክ እና ጄኔቫ ባሉ ከተማዎች ኑሮ በእጅጉ ውድ የሆነባቸው ከተሞች ናቸው፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም
