አሁንላይ የገቡትን አፀዋማት ተከትሎ በአትክልትና ጥራጥሬዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ለማድረግ ግብረሃይል ተቋቁሞ ወደስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።
በአሁኑ ወቅት በምርት ዋጋ ላይ ያለውን መጠነኛ የሆነ የዋጋ ንረት መሻሻሉን ያነሱት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሮክተሬት ዳይሬከተር የሆኑት አቶ ሰውነት አየለ፤ አሁንም የአፆማቱን መግባት ተከትሎ በማንኛውም የጥራጥሬና አትክልት ላይ ጭማሪ አዳይኖር ለማድረግ ጥብቅ ክትትል አየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬከተር ዳይሮክተሬት የሆኑት አቶ ሰውነት አየለ በፆሙ ወቅት ማህበረሰቡ የሚጠቀማቸውን ግብአቶች እጥረት እንዳይከሰት በመዲናዋ ውስጥ ባሉት 1መቶ72 የእሁድ ገበያዎችና በሌሎች የገበያ ስፋራዎች ከበቂ በላይ የሆነ ምርት እንዲገባ ተደርጓልም ብለዋል።
በመጨረሻም በማንኛውም ቦታ ላይ በምርቶች ላይ ጭማሪ ሲያደርግ የተገኘ ማንኛውም ነገዴ በዝምታ የማይታለፍ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሰውነት ማህበረሰቡ ጥቆማ በማድረግ ትብብር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
በልዑል ወልዴ
መጋቢት 03 ቀን 2016 ዓ.ም
