በኢትዮጵያ በግሉ የጤና ዘርፍ የመጀመርያ የሆነውን የኒውክሌር ሜዲስን ህክምና ማዕከል ተከፈተ።

ፓዮነር ዲያግኖስቲክ ማዕከል በኢትዮጵያ በግሉ ዘርፍ የመጀመርያ የሆነውን የኒውክሌር ሜዲስን መስጫ ማእከል መክፈቱን አስታውቋል።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ማዕከሉን ከፍተው ስራ አስጀምረዋል።

ሚኒስትሯ በምረቃ ስነስርአቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የጤና ዘርፊ በሽግግር ላይ እንደሚገኝ ተናግረው የግሉ የጤና ዘርፍ አስተዋጾ ከፍ እያለ ይገኛል።

አሁን ላይ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ለሀገራችን ዜጎች ፈተና እየሆኑ ናቸው ብለዋል።

እንደ ካንሰር የመሳሰሉ በሽታዎች የጤናውን ዘርፍ ክፉኛ እየፈተኑት እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ማዕከሉ የምርመራ ማዕከል ብቻ እንዳይሆን በምርምር ስራዎች ላይም ትኩረት አድርጎ እንዲሰራም ጠይቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፓዮነር ዲያግኖስቲክ ማዕከል የጤና ቱሪዝም ማዕከል እንዲሆን ጥረቱን አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክታቸውን እስተላልፈዋል።

ከዚህ በፊት ወደ ውጪ ሀገር ሔደው ህክምናውን ለማግኘት ይሔዱ የነበሩ ታካሚዎች በሀገራቸው ማግኘት ያስችላቸዋል ነው የተባለው።

ፓዮነር ዲያግኖስቲክ የኒውክሌር ሜዲስን ህክምና መስጠት የጀመረው አራት ኪሎ በሚገኘው አርሾ ሜዲካል ሴንተር ውስጥ ነው።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *