አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ለደንበኞቹ መኪና በብድር ለማቅረብ ከኢትዮ ፒካር ብራንደሰ ጋር መስማማቱን አስታወቀ

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር ከኢትዮ ፒካር ብራንድ ጋር ለደንበኞቹ መኪኖችን በብድር ለማቅረብ በዛሬው ዕለት ስምምነት ላይ ደርሷል።

መኪኖቹ በኤሌክትሪክ የሚሰሩና ለደንበኞች በብድር የሚሰጡ መሆናቸው ታውቋል።

በስምምነቱ መሠረት የአሚጎስ አባላት የሚፈልጓቸውን የኤሌክትሪክ መኪኖች ከ ኢትዮ ፒካር በብድር የሚሰጡ ይሆናል ተብሏል ።

በተጨማሪም ኢትዮ ፒካር ለአሚጎስ አባላትና መሥፈርቱን ላሟሉ የንስር ታክሲ ማህበር አባላት የመኪና ርክክብ አድርጓል ።

የ ሆን ዞ አውቶ ፋክተሪ የምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ ወኪል ኢትዮ ፒካር ብራንድ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ከዚህ ቀደም ከባንኮች ጋር በመተባበር አርባ ለሚሆኑ ደንበኞች በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን ማስረከቡንም አስታውሷል።

በአባቱ መረቀ

መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *