መልቲ ሚሊየነሩ ኤለን መስክ ዳኛዉ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲዘጉ ዉሳኔ ያሳለፉባቸዉን የትዊተር አካዉንቶች በድጋሚ እከፍታቸዋለሁ ማለቱን ተከትሎ ምርመራ ተከፍቶበታል፡፡
መስክ በኤክስ ገጹ ላይ የፍርድ ቤት ዉሳኔዉ ህገመንግስታዊ ባለመሆኑ ዕግዱን አንስቻለሁ ሲል ጽፏል፡፡
መስክ በተጨማሪም ዳኛዉ ስራ ይልቀቁ አልያም በወንጀል መጠየቅ አለባቸዉ ሲል አስፍሯል፡፡
ካምፓኒዉ ትዕዛዙን ለመቀበል ፍቃደኛ ካልሆነ ደግሞ 1መቶ ሺህ የብራዚል ገንዘብ የሚቀጣ ይሆናል ነዉ የተባለዉ፡፡
ዳኛዉ በዉሳኔያቸዉ ኤለን መስክ በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ላይ የተሳሳተ መረጃ ዘመቻን ከፍቷል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የኤክስ ዓለምዓቀፋዊ ጉዳዮች ቡድን ካምፓኒዉ የትኞቹ አካዉንቶች ገደብ እንደተጣለባቸዉ የገለጸዉ ጉዳይ የለም ብሏል፡፡
ባለፈዉ ዓመት የቀድሞዉ የብራዚል ፕሬዝዳንት ቦልሴናሮ ደጋፊዎች በአገሪቱን ኮንግረስ፣ በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት እና በፕሬዝዳንቱ ቤተመንግስት ላይ አመጽ በከፈቱበት ወቅት ረብሻዉን አስመልክቶ በኤክስ ገጻቸዉ ላይ የጻፉ ግለሰቦችን አካዉንት ሳይዘጉ እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡
ዳኛዉ በአገሪቱ ያሉ የተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾችን ለመገደብ ዉሳኔ ማሳለፋቸዉን ተከትሎም ዝናን አትርፈዋል፡፡
በተጨማሪም የቀድሞዉ ፕሬዝዳንት እና ደጋፊዎቻቸዉ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገዋል በሚልም ምርመራ እያካሄዱባቸዉ ይገኛሉ ሲል ቢቢሲ ዘጋቧል፡፡
እስከዳር ግርማ
መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም
