በቅርቡ በኢትዮጵያ የሚገኙ አበባ አልሚዎች ወደ አውሮፓ የሚልኩት ምርት ‘’የእሳት እራት’’ ከሚባለው አይነት ተባይ ነፃ ስለመሆኑ በጥንቃቄ እንዲያረጋግጡ ማሳሰቢያ መሰጠቱ ተሰምቷል።
በዚህም ህብረቱ በተደጋጋሚ ተባዩን ከኢትዮጵያ በሚላክለት አበባ ውስጥ ካገኘ፤ ዕገዳ ሊጥል ይችላል ተብሏል።
በጉዳዩ ላይ ጣቢያችን የኢትዮጵያ ሆርቲ ካልቸር አምራቾች እና ላኪዎች ማህበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ጋር ቆይታ አድርጓል፤
በእንግሊዝኛው ኤፍ ሲ ኤም(FMC) የተባለው ተባይ፤ የቢራቢሮ ዝርያ ያለው እና በእኛ ሀገር የእሳት እራት እንደሚባል አቶ ቴዎድሮስ አንስተዋል።

ወደ አውሮፓ ሲሄድ ግን በአየር ንብረት ምክንያት ባህሪውን እንደሚቀይር እና ተባዩ አውሮፓ ሲገባ ከመቶ በላይ የእጽዋት ዝርዋያችን ይበላል ይላሉ አቶ ቴዎድሮስ
ከሚላከው ምርት ምርመራ የሚደረግበት የናሙና መጠን ወደ 25 በመቶ ከፍ እንዲል ህብረቱ መወሰኑንም ተናግረዋል
ተባዩ የዛሬ ሁለት አመት በኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ የአበባ እርሻዎች ላይ መገኘቱን ግብርና ሚኒስትር መግለፁ ይታወሳል
አቶ ቴዎድሮስ እንደሚሉትም አበባ ላኪዎች ተባዩን ከእርሻቸው ለማስወገድ የተለያዪ ስራዎችና ስልጠናዎችም እየተሰጣቸው እንደሆነም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ አበባ ከ75 በመቶ በላይ መዳረሻው በአውሮፓ ህብረት በመሆኑ ምክንያት ተባዪን ለማስወገድ መስራት እንጂ ሌላ አይን መመልከት መፍትሄ አለመሆኑን አንስተዋል።
የአበባ ምርት ለኢትዮጵያ ከቡና ቀጥሎ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ መሆኑም ይታወቃል።
በለዓለም አሰፋ
መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም
