በሀገሪቱ ያለው የፀጥታ ችግር በአበባ ምርት ዘርፍ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል ተባለ

የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራቾች እና ላኪዎች ማህበር ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በሀገሪቱ ባለው ችግር የአበባው ዘርፍ እየተጎዳ እንደሆነ ገልፀዋል

በማንኛው ኢንቨስትመንት አስተማማኝ ሰላም ግድ ነው ያሉት ሀላፊው፤ የሰላም አለመኖሩ ለዘርፉ ትልቅ ችግር እንደሆነ ተናግረዋል

አቶ ቴዎድሮስ የሰላም እጦት ባለባቸው የአበባ ኢንቨስትመንቶች ላይ አሉታዊ የሚባል ተፅዕኖ ደርሶባቸውል ብለዋል

ምን ያህል ጒዳት በአበባ አልሚው ባለሀብት ላይ እንደደረሰ ባይነገርም ጉዳቱ ግን እንደታየ ተገልጿል።

በቅርቡ የአውሮፓ ህብረት በተለምዶ የእሳት እራት ተብሎ በሚጠራው ተባይ አበባው ምርት ላይ ተፅዕኖ እንዳሳረፈ አንስተው፤

ዘርፉ በብዙ እየተጎዳ ይገኛል ሲሉ አቶ ቴዎድሮስ ለጣቢያችን ገልፀዋል።

የአበባ ምርትን ወደ ዉጭ በመላክ ከአፍሪካ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትጠቀሰዉ ኢትዮጵያ በዓመት ከ200 እስከ 300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እንደምታገኝበት ይነሳል።

ለአለም አሰፋ

ሚያዚያ 01 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *